BBC News, አማርኛ - ዜና

ዜና

ቢቢሲ አማርኛ በቲክቶክ

አስተማማኝ ዜና እና መረጃን ቅድሚያ ለማግኘት ቢቢሲ አማርኛን ቲክቶክ ላይ ይከተሉ

የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ

የሰሜን ኢትዮጵያ ቀውስ

  • የፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ክልል ጦርነቱ መጠናቀቁን ገልጾ የባለአደራ አስተዳደር መመሥረቱን አስታወቀ

    በትግራይ ክልል ለስድስት ወራት የሚቆይ ባለ አደራ አስተዳደር ተቋቋመ። በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቋቋመው ይህ ባለአደራ አስተዳደር በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ነጻና ግልጽ ምርጫ በማከናወን ትግራይ የፌዴሬሽኑ አካል የምትሆንበትን ሁኔታ የማመቻቸት ኃላፊነት ተሰጥቶታል። በአስተዳደሩ ውስጥ በዋና አስፈጻሚነት ከተካተቱት መካከል የትግራይ ሰላም ኃይልን የሚመሩት ⁠ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር በየነ ይገኙበታል።

  • ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጋር በተያያዘ ባለፉት 5 ወራት አሜሪካ የወሰደቻቸው 5 እርምጃዎች

    ደም አፋሳሹ የትግራይ ጦርነት በፕሪቶሪያ ስምምነት አማካኝነት እንዲገታ ከፍተኛ ሚና ከነበራቸው አካላት መካከል የአፍሪካ ኅብረት እና አሜሪካ ይጠቀሳሉ። አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ ዋነኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ምዕራባውያን አገራት አንዷ ናት። የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከሳምንታት በፊት ዳግም ሲቀሰቀስ ቀድመው መግለጫ ካወጡ አገራትም አንዷ ናት። አሜሪካ ከጦርነት መነሳት በፊት እና በኋላ የወሰደቻቸውን እርምጃዎች እንደሚከተለው ቃኝተናል።

  • ሶማሊላንድ በግብፅ የተመሠረተውን ጥምረት በመቃወም ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆም ገለጸች

    ሶማሊላንድ የኢትዮጵያን ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል የትኛውንም ዓይነት ጣልቃ ገብነት እና ጥምረትን እንደምትቃወም ገለጸች። ነጻ አገርነቷን ያወጀችው ሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ ከጎረቤታቸው ኢትዮጵያ ጋር ባላቸው ትብብር ከፍተኛ መተማመን እንዳላቸው ገልጸው "የኢትዮጵያን መረጋጋት እና ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል የትኛውንም ጣልቃ ገብነት እንቃወማለን" ብለዋል።

  • 'በሕይወት እንተርፋለን አላልንም' ፡ በህወሓት ቁጥጥር ስር የቆዩት የቀድሞ ባለሥልጣናት ምን ገጠማቸው?

    የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ፣ አራት የቀድሞ ባለሥልጣናት ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ በህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር ከነበሩበት እስር አምልጠው በኢትዮጵያ ሠራዊት እጅ ከገቡ በኋላ ወደ መቀለ መመለሳቸውን ተናግረዋል። ባለሥልጣናቱ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በቀድሞ ጓዶቻቸው ከየቤታቸው ታግተው ከተወሰዱ በኋላ ያሳለፉትን እና እንዴት ሊያመልጡ እንደቻሉ ከመካከላቸው አንዱ ለቢቢሲ አጋርተዋል።

  • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩቢዮ ምን ተነጋገሩ?

    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በስልክ ተወያይተዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ፤ ንግግራቸው ከኤርትራ ጋር "እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት" የተመለከተ መሆኑ ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የውይይቱን ይዘት በዝርዝር ባይገልጹም "እጅግ ፍሬያማ" መሆኑን አስታውቀዋል።

  • ሶማሊያ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል በተፈጠረው ውጥረት ገለልተኛ መሆኗን ገለፀች

    የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ሐሰን ሞሐመድ አሊ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል በተፈጠረው ውጥረት አገራቸው "ገለልተኛ" መሆኗን ተናገሩ። ምክትል ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ከቢቢሲ ሶማልኛ ጋር እሁድ ጥቅምት 1/2019 ዓ.ም. በነበራቸው ቃለ ምልልስ ወቅት ነው።"የሶማሊያ መንግሥት አቋም ሰላማዊ እና ገለልተኛ ነው" ያሉት ሚኒስትሩ ከአገራቱ ጋር ታሪካዊ፣ መልክዓ ምድራዊ እንዲሁም ሃይማኖታዊ ትስስር እንዳለ ተናግረዋል።

  • ወደ ትግራይ የተጓዙት የፌደራል መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ምን አሉ?

    በትግራይ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ተቋርጦ የነበረው የአውሮፕላን በረራ በትናንትናው ዕለት ሲጀመር የፌደራል መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ወደ መቀለ እና አዲግራት በማምራት ነዋሪዎችን ማግኘታቸውን ገልጸዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ ከ18 ወራት በኋላ ወደ ክልሉ ዋና መዲና መመለሳቸውን ሲናገሩ፣ ዶ/ር አብርሃም በላይ ደግሞ "ሰላም የተጠማው ሕዝባችንን ጎበኘነው” ብለዋል። የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው በመቀለ እና አዲግራት በነበራቸው ቆይታ "ጥልቅ የሰላም ጥማት" ማየታቸውን ገልጸዋል።

  • ስለ ሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መንግሥት ለምን ዝምታን መረጠ? የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ?

    በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት ሁለት ሳምንት አልፎታል፤ የፌደራሉ መንግሥት እና አጋር ኃይሉ መቀለን እና ሌሎች የትግራይ አካባቢዎችን ተቆጣጥረዋል። ከጦርነቱ ጅማሮ አንስቶ ተሳታፊ እንደሆኑ ሲነገር የነበረው የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በብዛት ወደ ትግራይ መግባታቸው ተዘግቧል። ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ ባድረጉት ንግግርም ሆነ መንግሥታቸው ስለ ጦርነቱ እስካሁን በይፋ ያሉት ያሉት ነገር የለም፤ ለምን?

  • ስለ ሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከዲፕሎማሲ ውዝግብ እስከ ፀጥታው ምክር ቤት አቤቱታ እስካሁን የምናውቀው

    ሁለት ሳምንት ያለፈው በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ጦርነት እንደቀጠለ ነው። በዚህ ሳምንት የጦርነቱ ዋነኛው ጉዳይ የኤርትራ ወታደሮች ከድንበር በሻገር በብዙ ኪሎ ሜትሮች ርቀው ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባታቸው ነው። ይህም ኢትዮጵያ ወረራ እንደተፈጸመባት በመግለጽ ለመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ደብዳቤ እንድትጽፍ አድርጓታል። እስካሁን በተፈጠረው ቀውስ ዙሪያ ስላሉ ዋና ዋና ሁኔታዎች ምን እናውቃለን?

  • ትግራይ በኮማንድ ፖስት እንደምትመራ እና ከስድስት ወር በኋላ ምርጫ እንደሚካሄድ ተነገረ

    የህወሓት መሪዎች መቀለን ጨምሮ ከበርካታ የትግራይ ከተሞች ለቅቀው ከወጡ በኋላ ክልሉ በፌደራል መንግሥቱ ኮማንድ ፖስት ሥር እንደሚቆይ እና በትግራይ ምርጫ እንደሚካሄድ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ። የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት እና በአሁኑ ጊዜ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ይህንን የተናገሩት ቲቢኤስ ከተባለ መገናኛ ብዙኃን ጋር በትግርኛ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።

የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?

የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!

የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች

ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ

አነጋጋሪ ጉዳይ

ከየፈርጁ

አጃኢብ!

የተመለሱ ጥያቄዎች

ሌላ ዕይታ

በስፋት የተነበቡ