
የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የምስሉ መግለጫ, የዩክሬን፣ የሩሲያ እና የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በዩክሬን ጦርነት ላይ እየተካሄደ ያለውን ውይይት ለመቀጠል ረቡዕ ለሁለተኛ ቀን በድጋሚ ይሰበሰባሉበዩክሬን እና በሩሲያ መካከል በአቡዳቢ እየተካሄደው ያለው የሦስትዮሽ ውይይት የመጀመርያ ቀን ውጤታማ እንደነበር ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ተናገሩ።
ከኪየቭና
ከሞስኮ የመጡ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አራት ሰዓታት ከፈጀው ውይይት በኋላ ስለ ንግግሩ ዝምታን ቢመርጡም፣ በውይይቱ ያልተሳተፉት ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ግን ውይይቱ “ገንቢና በጣም ጥልቅ ይዘት ያለው” እንደነበር ተናግረዋል።
ፓሪስ
ያሉት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በበኩላቸው ስብሰባው “እጅግ ፍሬያማ” እንደነበረ ገልጸዋል።
በሩሲያ እና
በዩክሬን መካከል እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ለማስቆም የሚያበቃ ጉልህ ውጤት ከዚህ ውይይት ይገኛል
የሚለው ተስፋ ዝቅተኛ ቢሆንም፣ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ከዚህ ቀደም ሞስኮና ኪየቭ ከጦርነቱ በኋላ የዩክሬንን ምሥራቃዊ ክልሎች ማን
ይቆጣጠረው በሚለው ጉዳይ “አንዳንድ መለሳለሶች” እያሳዩ መሆኑን ገልጸው ነበር።
ዜሌንስኪ የሰብዓዊ ጉዳዮች የጦር ምርኮኞችን እንደመለዋወጥ ያሉ ጉዳዮች ተነስተው
መወያየታቸውን ተናግረዋል።
ማክሰኞ
ዕለት በሁለቱ አገራት መካከል ውይይቱ ሲጀመር የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቤተሰብ
አባል የሆኑት ጃሬድ
ኩሽነር ለተሳታፊዎች ዝርዝር መረጃ ሳይሰጡ አሜሪካ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያሉትን
ልዩነቶች “ማጥበብ ችላለች” ብለዋል።
በተጨማሪም “ጦርነቱን ያስቆማል ተብሎ የሚታሰብ መፍትሔ” ላይ
ይደረሳል ተስፋ
እንዳላቸው ተናግረዋል።
ኩሽነር
ከዚህ ቀደም ውይይቶቹ “ከጦርነት በኋላ የደኅንነት ስጋቶችን” በመፍታት ላይ እንደሚያተኩሩ ገልጸው ነበር።
በኋላ
ላይም በኮፐንሃገን ስለ አሜሪካ ባለሥልጣናት የድርድር አቀራረብ የተጠየቁት ዜሌንስኪ “ለውጦችን እያየሁ ነው። የምሰማው ነገር በጣም አስደስቶኛል” ብለዋል።
ጃሬድ ኩሽነር እና የትራምፕ የሰላም ልዑክ ስቲቭ ዊትኮፍ ከዋናው ስብሰባ ጎን
ለጎን ከዩክሬን፣ ከአውሮፓ እና ከኔቶ ባለሥልጣናት ጋርም ተገናኝተው ተወያይተዋል።
እስካሁን ድረስ የአውሮፓ መሪዎች ከሰላም ድርድሮቹ ውጭ ተደርገው ቆይተዋል።
ሆኖም ስለ አህጉራቸው ደኅንነት የሚወሰኑ ውሳኔዎች ያለ እነርሱ ተሳትፎ እንዳይወሰኑ በመስጋታቸው በውይይቱ ውስጥ እንዲካተቱ ግፊት
ሲያደርጉ ቆይተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በፓሪስ በነበራቸው ጉብኝት ወቅት አውሮፓውያን “ይህንን
ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የመፍትሔው አካል ናቸው” በማለት
ተናግረዋል።
ሆኖም
አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን “ሩሲያውያን ከአውሮፓውያን ጋር በተያያዘ ጥሩ ልምድ የላቸውም” ብለዋል።
የአውሮፓ
ኅብረት ባለሥልጣናት የሚደግፏቸው አንዳንድ ሐሳቦች፣ ያለ ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የሚጠይቁ ሐሳቦችን ጨምሮ በሞስኮ በተደጋጋሚ ውድቅ ይደረጋሉ።
የሩሲያ
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ማክሰኞ ዕለት የተኩስ አቁም ስምምነት ዩክሬን እንደገና ራሷን እንድታደራጅ ዐዕድል ይሰጣታል በማለት “ይህንን አንቀበለውም” ሲሉ ተናግረዋል።
በአጠቃላይ
ሞስኮና ኪየቭ ግጭቱን ለማቆም በሚያስችሉ ዋና ጉዳዮች ላይ አሁንም ከፍተኛ የአቋም ልዩነት አላቸው።