የሱዳን መንግሥት በገዳሪፍ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ቆንስላ ዘጋ

ሱዳን በገዳሪፍ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ቆንስላ መዝጋቷን እና ዲፕሎማቶቹን ማስወጣቷን ሮይተርስ የዜና ወኪል ሁለት ምንጮችን ጠቅሶ ዘገበ። ሱዳን ይህንን እርምጃ የወሰደችው ኢትዮጵያ ስድስት የሱዳን ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓታት ውስጥ አገሪቱን ለቅቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ መስጠቷን ተከትሎ ነው።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

የሶማሊያ የባሕር ላይ ወንበዴዎች የኢራንን አሳ አጥማጅ መርከብ በቁጥጥራቸው ሥር አዋሉ

የሶማሊያ የባሕር ላይ ወንበዴዎች 23 ሰዎችን የጫነች የኢራን አሳ አጥማጅ መርከብ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰማ።

የሕንድ ውቅያኖስ የባሕር ላይ ደህንንት ማዕከል የባሕር ላይ ወንበዴዎቹ የንግድ መርከቦችን በመጠጋት ተጨማሪ ጥቃት ሊፈጽሙ ይችላሉ ሲል አስጠንቅቋል።

አዚኒ የተባለችው የአሳ አጥማጅ መርከብ የታገተችው ሐሙስ ዕለት መሆኑ ታውቋል።

መርከቧ በሰሜን ምሥራቅ ሶማሊያ በባንዳር ባይላ እና ሀፉን ከተሞች መካከል እየቀዘፈች እንደነበር የፑንትላንድ የባሕር ላይ ፖሊስ እሁድ ዕለት አስታውቋል።

የፖሊስ ባልደረባው የፈረንሳይ ዜና ወኪል (ኤኤፍፒ) እነደተናገረው 12 የባሕር ላይ ወንበዴዎች 21 ኢራናውያንን እና ሁለት ሶማሊያውያን ጸጥታ ባልደረቦችንን ያሳፈረችውን መርከቧን አግተዋል።

ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ለመስጠት ኃላፊነት እንዳልተሰጠው በመግለጽ ስሙ አንዳይገለጽ የጠየቀው ይህ ግለሰብ የመርከበኞቹ ደህንነት በምን ሁኔታ ላይ እንደሆነ አይታወቅም ብሏል።

የባሕር ኃይል ደህንነት ማዕከሉ ባወጣው ተጨማሪ ማስጠንቀቂያ ወንበዴዎቹ ያገቱትን መርከብ ተጠቅመው በንግድ መርከቦች ላይ ተጨማሪ ጥቃት ሊሰነዝሩ ይችላሉ ብሏል።

የአውሮፓ ኅብረት የባሕር ኃይል ዘመቻ ጉዳዩን እየመረመረ መሆኑን ገልጾ በአካባቢው የሚገኙ መርከቦች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን እንዲያሳውቁ ጥሪ አቅርቧል።

ይህ የመርከብ እገታ የተከሰተው በኤደን ባሕረ ሰላጤና በምዕራባዊ ሕንድ ውቅያኖስ አካባቢ የሶማሊያ ባሕር ወንበዴዎች እንደገና ካንሰራሩ በኋላ ነው።

ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ይፋ በተደረገ መረጃ መሠረት ከሚያዝያ ወር ጀምሮ ስድስት የንግድ መርከቦች ታግተዋል።

ከእነዚህም ጥቃቶች አንዳንዶቹ ከሶማሊያ የባሕር ዳርቻ በጣም ርቀው በሚገኙ ስፍራዎች የተፈጸሙ ናቸው።

በመስከረም ወር የፑንትላንድ ባለሥልጣናት እንደገለጹት፣ ወንበዴዎቹ ኤምቲ ኦነር 25 በመባል የምትጠራውን ነዳጅ ጫኝ መርከብ ካገቱ በኋላ የጸጥታ አባላት ከመድረሳቸው በፊት አምስት ባሕረተኞችን ገድለዋል።

የነዳጅ ጫኝ መርከቡ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ በወንበዴዎች እጅ ነበር። ባለሥልጣናት 16 በባሕር ላይ ውንብድና የተጠረጠሩ ግለሰቦች መታሰራቸውን ገልጸዋል።

ባለፉት አስር ዓመታት ዓለም አቀፍ የባሕር ኃይል ጥበቃዎች እና የባሕር ደህንነት ማሻሻያዎች በሶማሊያ አካባቢ የባሕር ላይ ውንብድናን በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሰውት ነበር። ነገር ግን በቅርቡ የተፈጸሙት የመርከብ እገታዎች በአገሪቱ ረዥም የባሕር ዳርቻ አካባቢ በሚያልፉ መርከቦች ላይ የደህንነት ስጋት ደቅነዋል።