በአለም ላይ ያሉ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች የልደት በዓል አከባበር በምስል

ታትሟል

በኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ሩሲያን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ያሉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የእየሱስ ክርስቶስ ልደት (የገና በዓልን) በዛሬው ዕለት ታህሳስ 29 እያከበሩ ይገኛሉ። የተወሰኑትን አገራት በዓል አከባበር በምስል እነሆ

የቦስኒያ ኦርቶዶክስ ቄስ ማርኮ ማሌስ በኦርቶዶክስ የገና ዋዜማ ላይ በዜኒካ፣ ቦስኒያ እና ሄርዞጎቪና በምትገኘው የሆሊ ማዘር ኦፍ ጋድ [ማርያም} ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ እየመሩ በነበረበት ወቅት
የምስሉ መግለጫ, የቦስኒያ ኦርቶዶክስ ቄስ ማርኮ ማሌስ በኦርቶዶክስ የገና ዋዜማ ላይ በዜኒካ፣ ቦስኒያ እና ሄርዞጎቪና በምትገኘው የሆሊ ማዘር ኦፍ ጋድ [ማርያም} ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ እየመሩ በነበረበት ወቅት
የኢየሩሳሌም የግሪክ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ ሳልሳዊ በምስራቅ ኦርቶዶክስ የቀን መቁጠሪያ መሰረት ገናን ለማክበር ወደ ቤተልሔም የክርስቶስ ልደት ቤተክርስቲያን ያቀኑ ሲሆን በደረሱበት ወቅት ፈገግ ብለው ታይተዋል።
የምስሉ መግለጫ, የኢየሩሳሌም የግሪክ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ ሳልሳዊ በምስራቅ ኦርቶዶክስ የቀን መቁጠሪያ መሰረት ገናን ለማክበር ወደ ቤተልሔም የክርስቶስ ልደት ቤተክርስቲያን ያቀኑ ሲሆን በደረሱበት ወቅት ፈገግ ብለው ታይተዋል።
በርካቶችም የግሪክ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ ሳልሳዊን መምጣት በጉጉት ሲጠባበቁ ነበር
የምስሉ መግለጫ, በርካቶችም የግሪክ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ ሳልሳዊን መምጣት በጉጉት ሲጠባበቁ ነበር
ርችቶች በዜኒካ፣ ቦስኒያ እና ሄርዞጎቪና ውስጥ በምትገኘው የሆሊ ማዘር ቤተ ክርስስቲያን በላይ ታይቷል
የምስሉ መግለጫ, ርችቶች በዜኒካ፣ ቦስኒያ እና ሄርዞጎቪና ውስጥ በምትገኘው የሆሊ ማዘር ቤተ ክርስስቲያን በላይ ታይቷል
በሰርቢያ ዋና ከተማ ቤልግሬድ ነዋሪዎች በሴንት ሳቫ ቤተመቅደስ ፊት ለፊት በነበረው የችቦ ማቃጠል ስነ ስርዓትን ሲያከብሩ
የምስሉ መግለጫ, በሰርቢያ ዋና ከተማ ቤልግሬድ ነዋሪዎች በሴንት ሳቫ ቤተመቅደስ ፊት ለፊት በነበረው የችቦ ማቃጠል ስነ ስርዓትን ሲያከብሩ
የሩስያ ፓትርያርክ ኪሪል በዋና ከተማዋ ሞስኮ በሚገኘው ክራይስት ዘ ሴቪየር ካቴድራል የነበረውን የልደት አገልግሎት መርተዋል።
የምስሉ መግለጫ, የሩስያ ፓትርያርክ ኪሪል በዋና ከተማዋ ሞስኮ በሚገኘው ክራይስት ዘ ሴቪየር ካቴድራል የነበረውን የልደት አገልግሎት መርተዋል።
ሩሲያ በዓለም ላይ ከፍተና ቁጥር ያለው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ያላት አገር ናት
የምስሉ መግለጫ, ሩሲያ በዓለም ላይ ከፍተና ቁጥር ያለው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ያላት አገር ናት
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሴቪየር ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ሻማ በማብራት በዓሉን አክብረዋል
የምስሉ መግለጫ, የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሴቪየር ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ሻማ በማብራት በዓሉን አክብረዋል
የኮፕት ክርስቲያኖች ወደ 2,000 ለሚጠጉ ዓመታት በግብፅ ኖረዋል። የግብፅ ኮፕቲክ ካህናት በካይሮ በሚገኘው ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የልደት በዓል ቅዳሴን እያከናወኑ
የምስሉ መግለጫ, የኮፕት ክርስቲያኖች ወደ 2,000 ለሚጠጉ ዓመታት በግብፅ ኖረዋል። የግብፅ ኮፕቲክ ካህናት በካይሮ በሚገኘው ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የልደት በዓል ቅዳሴን እያከናወኑ
የሶሪያ ክርስቲያኖች በደማስቆ በሚገኘው ማር ሳርኪስ የአርመን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሻማ አብርተዋል።
የምስሉ መግለጫ, የሶሪያ ክርስቲያኖች በደማስቆ በሚገኘው ማር ሳርኪስ የአርመን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሻማ አብርተዋል።
የግሪክ ኦርቶዶክስ ተከታዮች በኢስታንቡል በነበረው የውሃ የበረከት ሥነ ሥርዓት ላይ መስቀል እየተሳለሙ።
የምስሉ መግለጫ, የግሪክ ኦርቶዶክስ ተከታዮች በኢስታንቡል በነበረው የውሃ የበረከት ሥነ ሥርዓት ላይ መስቀል እየተሳለሙ።
በባኩ፣ አዘርባጃን በሚገኘው የቅዱስ ማይርቤየርስ ካቴድራል ውስጥ እየጸለየች ያለች ሴት
የምስሉ መግለጫ, በባኩ፣ አዘርባጃን በሚገኘው የቅዱስ ማይርቤየርስ ካቴድራል ውስጥ እየጸለየች ያለች ሴት