በአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ ታሪክ የሠሩ የአፍሪካ የዘር ሐረግ ያላቸው ፖለቲከኞች

ሜላት ኪሮስ መድረክ ላይ ንግግር እያደረገች
የምስሉ መግለጫ, አዲስ አበባ የተወለደችው ሜላት ኪሮስ ወደ አሜሪካ ዴንቨር የሄደችው ሕፃን እያለች ነው
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ

በአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ በዲሞክራቶች የድል ድግስ ላይ ተሰምቶ የማይታወቅ ሰላምታ ተሰማ።

ይህ ፈገግ ያሰኘ ሰላምታ የቀረበው ከግብፅ ስደተኞች ከተወለደው የ42 ዓመቱ አብዱል ኤል-ሳይድ ነው።

ኤል-ሳይድ ተፎካካሪያቸውን ደግፈው የምርጫ ዘመቻ ላደረጉት እና ጥር ላይ የሚሽገን ሴናተር (የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል) ሲሆኑ ቃለ መሀላ ለሚያስፈፅሟቸው ምክትል ፕሬዘዳንት ጄዲ ቫንስ ነበር ሰላምታውን ያቀረቡት።

አሜሪካ የተወለዱት ፖለቲከኛው አብዛኛውን የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን ያሳለፉት 'ሙስሊም ወንድማማቾችን ይደግፋሉ' በሚል ከወግ አጥባቂዎች እና ከፕሬዝዳንት ትራምፕ የደረሰባቸውን ጥቃት በመከላከል ነው።

ኤል-ሳይድ ክሱን ውድቅ ያደርጋሉ።

ድላቸውን ለማብሰር ለተሰባሰበው ደጋፊያቸው በግብፅ የአረበኛ ቅላፄ "ስሜ አብዱል ራህማን ሞሐመድ ኤል-ሳይድ ነው" አሉ።

አረብኛ የሆነው የሙስሊም ስማቸው በተቃዋሚያቸው ዘንድ ዒላማ ተደርጓል።

ማክሰኞ በተደረገው የአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ ያሸነፉት ኤል-ሳይድ የመጀመሪያዊው ሙስሊም የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል (ሴናተር) ሆነዋል።

ኤል-ሳይድ ማኅበራዊ የትስስር ገፆች ላይ ያተኮረ የምረጡኝ ዘመቻ አድርገዋል። በተለይም በቲክቶክ 'የጀን ዚ' ቀልዶችን አዋዝተው በቀጥታ ለወጣት መራጮች ቀርበዋል።

የቀድሞው የኅብረተሰብ ጤና አስተዳደር ባለሥልጣን የምርጫ ዘመቻ ለሁሉም የጤና መድኅን፣ አቅምን የሚመጥን ቤት እና በፖለቲካ ላይ ኮርፖሬቶች ያላቸውን ተፅዕኖ መቀነስ ያሉ ተራማጅ ሀሳቦች ላይ ያጠነጠነ ነበር።

ፖለቲከኛው የአሜሪካ ጦር ለእስራኤል የሚሰጠውን እርዳታም ክፉኛ ተችዋል።

ይሁን እንጂ ኤል-ሳይድ ብቻቸውን አይደሉም።

አሜሪካዊ ፖለቲከኛ አቡዱል ኤል-ሳይድ
የምስሉ መግለጫ, አሜሪካዊ ፖለቲከኛ አቡዱል ኤል-ሳይድ
Skip podcast promotion and continue reading
BBC News Amharic የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ!
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

ከትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኮንግረስ ተመራጭ እስከ የናይጄሪያ የዘር ሀረግ ያላቸው ተመራጭ፤ በርካታ የአፍሪካ የዘር ግንድ ያላቸው ፖለቲከኞች የዘንድሮውን የአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ አሸንፈዋል።

በፕሬዝዳንት የሥልጣን ዘመን አጋማሽ ላይ የሚደረገው የአሜሪካ ምርጫ አሜሪካዊያንን በሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (ኮንግረስ) ባሻገር በግዛቶች እና በአካባቢ የሚወክሉት የሚወሰንበት ነው።

የ29 ዓመቷ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሜላት ኪሮስ በአሜሪካ ኮንግረስ የተመረጠች የመጀመሪያዋ 'ጄን ዚ' (እ.አ.አ ከ1997 እስከ 2012 የተወለደ ትውልድ) ሆናለች።

ኢትዮጵያ የተወለደችው ሜላት ሕፃን እያለች ወደ አሜሪካ አቅንታ ዴንቨር አድጋለች።

ተመርጣ ሥልጣን ይዛ የማታውቀው ሜላት በዲሞክራቶች ቅድመ ምርጫ በኮሎራዶ የመጀመሪያ ድስትሪክት (የምርጫ ወረዳ) ለ15 የሥልጣን ዘመን ያገለገሉትን ፖለሪከኛ አሸንፋ ነበር እጩ የሆነችው።

ማክሰኞ ዕለት በተረገው ምርጫ ደግሞ በከፍተኛ ድምፅ አሸንፋለች።

ሜላት እንደ ኤል-ሳይድ ሁሉ የምርጫ ዘመቻዋን ያካሄደችው ለወጣት ተራማጅ መራጮች ቀዳሚ በሆኑ ጉዳቶች ላይ ነው። የኑሮ ውድነት፣ የሕፃናት እንክብካቤ እና ሕክምና እንዲሁም ለሁሉም የጤና መድኅን ዘመቻ ያደረገችባቸው ጉዳዮች ናቸው።

ከአሜሪካ ዲሞክራት ሶሻሊስት ድጋፍ ያገኘችው ሜላት ጥርስ ውስጥ የገባው የአሜሪካ የኢምግሬሽን እና ጉሙሩክ ባለሥልጣን (አይስ) እንዲዘጋ እንዲሁም አሜሪካ ለእስራኤል የምትሰጠውን ድጋፍ እንድታቋርጥ ጥሪ አቅርባለች።

ሜላት ኪሮስ እስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርገውን ጦርነት በተደጋጋሚ መተቸቷ ውዝግብ አስነስቶባታል።

ትችቷ የእስራኤል አገር ላይ እንጂ አይሁዳዊያን ላይ አይደለም በሚልም ሜላት አቋሟን ግልፅ አድርጋለች።

እ.አ.አ በ2023 የጠበቃ ቢሮዎች ለሕግ ትምህርት ቤት ዲኖች ፍልስጤምን የሚደግፉ ሰልፎች ሲካሄዱ በካምፓስ ፀረ ሴማዎነት ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ማሳሰባቸውን ተከትሎ ለቢሮዎቹ ግልፅ ደግዳቤ ፅፋለች። ይህን ደብዳቤ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆኗም በኒው ዮርክ ትሰራበት ከነበረው ትልቅ የጠበቃ ቢሮ ተባርራለች።

ሜላት ፀረ ሴማዊነትን የምታወግዝ ቢሆንም እርሷ ትሰራበት የነበረውን ጨምሮ የጠበቃ ቢሮዎች የእስራኤል ቅቡልነት ለማስጠበቅ የሚደረግ አክራሪነት ታስጠነቅቃለች።

ስለ ፖለቲካ በአጠቃላይ በቁም ነገር ማሰብ የጀመረችው ከሥራዋ ከተባረረች በኋላ መሆኑን ትናገራለች።

አድሪያን ቦፎ በምርጫ ዘመቻቸው
የምስሉ መግለጫ, አድሪያን ቦፎ በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሁለተኛ ትውልድ ጋናዊ አሜሪካዊ የሆነው አድሪያን ቦፎ የሜሪላንድን 5ተኛ ድስትሪክት ይወክላል።

የ32 ዓመቱ ፖለቲከኛ ቨርጅኒያ ተወልዶ ፕሪንስ ጆርጅ ካውንቲ ሜሪላንድ አድጓል። ወላጆቹ ከጋና ወደ አሜሪካ የመጡ ስደተኞች ናቸው።

በተለያዩ የአካባቢያው ኃላፊነቶች የቆየው ቦፎ የምርጫው ዘመቻው በሺዎች የሚቆጠሩ የፌደራል ሠራተኞች በሚኖርበት ግዛት ዋነኛ በተባሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር።

ወደ አሜሪካ ኮንግረስ በድጋሚ ከተመለሱት ውስጥ የሶማሊያ ተወላጅ የሆኑት ኢልሃን ኦማር ይገኙበታል። የ44 ዓመቷ ፖለቲከኛ የፌደራል ምርመራ የተከፈተባቸው ቢሆንም ለአምስተኛ ጊዜ ተመርጠዋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ እ.አ.አ በ2018 ለኮንግረስ የተመረጡት ኢልሃን በምክር ቤት የተመረጡ የመጀመሪያዋ ሶማሊ-አሜሪካዊት እና ሙስሊም ሴት ናቸው።

በዶናልድ ትራምፕ የዘወትር ዒላማ ሲሆኑም ፕሬዝዳንቱ እርሳቸውን እና ሌሎች የሶማሌ ስደተኞችን በተደጋጋሚ ተችተዋል።

ሌሎች የአፍሪካ የዘር ግንድ ያላቸው ፖለቲከኞችም በግዛት እና በሌሎች የፖለሪካ ሥልጣኖች ድል ቀንቷቸዋል።

ናይጄሪያ የተቀለዱት ጁኔር ኢዞኑ ለቴክሳስ የምክር ቤት ተመርጠዋል።

ሌላኛዋ የናይጄሪያ ተወላጅ የ34 ዓመቷ ካሮል ካዚማ በፔንሴቬኒያ ግዛት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ወንበራቸውን አስጠበቀዋል።

ቢያንስ አራት የናይጄሪያ የዘር ሀረግ ያላቸው ፖለቲከኞች በዘንድሮው የአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ አሸንፈዋል።

ከአትላንቲክ ውቅያኒስ ማዶ ይህን ለሚያዩ አፍሪካዊያን ወጣቶች ድሉ አዲሱ ትውልድ በአገሩ ምን ሊያሳካ እንደሚችል ነፀብራቅ የሰጠ ነው።